Technologies Technologies

አይባር ሁለገብ ቦይና መደብ ማውጫ/Aybar BBM

ከብረት የተሰራ የራሱ የብረት ዘንግ ድግር አንዲሁም ሁለት ክንፎች ያሉት ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጥ መሣሪያ ነው:: ከነዚህም ጥቅሞች መካከል ኮትቻ አፈርን ማጠንፈፍ ፣የዝናብ ውሃን በማቆር የአፈር እርጥበትን ማሻሻል ፣ ዘር ማልበስ፣ ቦይ ማውጣት ይገኙበታል።

በርበሬ ማድረቂያ

ይህ መሳሪያ የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም በርበሬን በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እና ፍጥነት በማድረቅ በቀላሉ እንዲልም ያደርጋል፡፡

የፕላስቲክ ውጤቶችን የሚቆራርጥ ማሽን

ይህ መሳሪያ በተለያየ ቦታ የተሰበሰቡ ፕላስቲኮችን በመቆራረጥ ለመልሶ ማዋል ለማዘጋጀት ያገለግላል፡፡

የብረት በር መዝጊያ

ይህ ፈጠራ ቁልፍ ለመቀረፅ ልዩ ክህሎት ከማስፍልጉ በተጨማሪም ከውስጥ ከተዘጋ አለመከፈቱ ልዩ ያደርገዋል፡፡

የዶሮ መዳጫ

የዶሮን ላባ ለማስለቀቅ ይህ መሳሪያ በኤሌክትሪክ ሞተር እየተሽከረከረ ፊሸሩ ባለበት አልሙኒየም ሺት የዶሮ ላባ ይገነጥላል፡፡

የወተት መናጫ(በእግር ፔዳል የሚሰራ)

ይህ መሳሪያ ወተትን በቀላሉ እና በፍጥነት ለመናጥ የሚያገለግል ሲሆን የሚሰራው ተጨማሪ ሀይል ሳይጠይቅ በእግር ብቻ በሚገፋ ፔዳል የሚሰራ ነው፡፡