Back

ከፕላስቲክ ተረፈ ምርት የሚገኝ ኮንክሪት

ከፕላስቲክ ተረፈ ምርት የሚገኝ በከፊል አሸዋን ሊተካ የሚችል አስተማማኝ ኮንክሪት ተሰራ

በባዝ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ምሁራን ከህንድ ተማራማሪዎች ጋር በመተባበር ከባቢ አየርን የማይጎዳ ከፕላስቲክ ቆሻሻ በከፊል አሸዋን ሊተካ የሚችል ኮንክሪትን አጎልብተዋል፡፡

በህንድ የግንባታው ዘርፍ እየተስፋፋበት ባለበት ሁኔታ አሸዋን ለማግኘት በወንዞች የሚደረገው ፍለጋ ከወትሮው በተለየ ጨምሯል፡፡ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ የህንድ ከተሞች አሸዋን ከወንዞች ማውጣት ታግዷል፡፡

አሸዋ ውሃ አካባቢ ለሚበቅሉ እፅዋት አስፈላጊ ሲሆን እነዚህ እፅዋት ለደኖችና ለብዝሃ ህይወት ምርታማ የሆነን ስፍራ ያመቻቻሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ጎርፍ በሚከሰትበት ግዜ ጨዋማ ውሃ ወደ መሬት ውስጥ ዘልቆ እንዳይገባ ይከላከላሉ፡፡

የህንድ ፈጣን እድገት ያመጣው ሌላው ችግር ባልተጠበቀ ሁኔታ ለእቃ መያዣና ማሸግያነት የሚውሉ የፕላስቲክ ውጤቶች ከግልጋሎት በኋላ በመሬት ተቀብረው መገኘታቸው ነው፡፡

ሁለቱንም ችግሮች ለመፍታት(ለግንባታ የአሸዋን እጥረትንና የፕላስቲክ ቆሻሻ ዎች መብዛትን) የፕሮጀክቱ ቡድን 10 በመቶ የሚሆነውን አሸዋ ተክቶ ለመስራት የሚያስችል ኮንክሪትን ችለዋል፡፡

በተጨማሪም ምርምሩ ፕላስቲኩ በአሸዋው ቦታ መተካቱ የኮንክሪቱን ጥንካሬ፣ ዘላቂነቱን፣ እሳትንና ውሃን የመቋቋም አቅሙን ያጠናል፡፡

ዶክተር ጆን ኦር ከሲቪል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመነት እንዳሉት "የፕላስቲክ ቆሻሻዎችን መልሶ በመጠቀም በተመለከተ የሚደረገው ጥናት ጠቃሚና ሊያድግ የሚችል ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዜናው በሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃ ማዕከል ተዘጋጀ

ምንጭ፡ phys.org